IOM/ETHIOPIA ለብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የተሽከርካሪዎች ድጋፍ አደረገ!
ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ IOM/ETHIOPIA የኮሚሽኑን አቅም ግንባታ ጥረት በመደገፍ ያደረገውን የሁለት ቶዮታ Station wagon ተሽከርካሪዎች ልገሳ ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ተረክበዋል። በኮሚሽኑ ቅጥር ለተደረገው የቁልፍ ርክክብ ሥነ – ስርዓት ላይ የIOM/ETHIOPIA የፕሮግራም ዋና ኃላፊ የሆኑት Mr. Emran GULER ተገኝተው ርክክቡን ፈፅመዋል። በርክክቡ ወቅት ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ስራውን ከጀመረ ከግማሽ ዓመት ያላለፈና በዚህ ወቅት ተቋማዊ አደረጃጀት ፈጥሮ እያጠናከረና ስራውንም ጎን ለጎን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ኮሚሽኑ ለሰላም ሂደቱ የተሰጠውን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት በአቅም ግንባታ ረገድ እያደረገ ላለው ጥረት አጋር ድርጅቶች በየደረጃው እያደረጉ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ IOM ከወራት በፊት ካደረገው የቴክኒክና ማቴሪያሎች ድጋፍ በተጨማሪ አሁንም እነዚህን ሁለት ተሽከርካሪዎች በመለገሱ አመስግነው የአጋርነትና የትብብር ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። የIOM/ETHIOPIA የፕሮግራም ዋና ኃላፊ Mr. Emran GULER በበኩላቸው IOM ኮሚሽኑ እየተገበረ ላለው የDDR ፕሮግራም መሳካት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።