የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ለቀድሞ ተዋጊዎች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!!!

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ብር 51,000,000 ዋጋ ያላቸው አልባሳት፣ ጫማዎችና ለቀለብ የሚሆኑ ምግቦች ለኮሚሽናችን ልገሳ አደረገ። የተለገሱት ቁሳቁሶችና ምግቦች ኮሚሽኑ በአገሪቱ ባሉት የተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚገኙ ሲሆን፣ ርክክቡ ሐዋሳና አዋሽ ቅ/ጽ/ቤቶቹ ከሚገኙት ነሐሴ 30 እና ጳጉሜ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጀምሯል። በዚሁ መሰረት ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ሐዋሳ ከሚገኘው የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ብር 22,800,000 ዋጋ የሚያወጡ አልባሳት እንዲሁም ጳጉሜ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. አዋሽ ሰባት ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤት ብር 15,200,000 ዋጋ የሚያወጡ አልባሳትን የኮሚሽናችን ተወካይ አቶ ሽመልስ በላሶ ተረክበው በቀጥታ ለትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች አገልግሎት እንዲውል ወደ ትግራይ ክልል ተልኳል። በቀጣይም ቀሪ ቁሳቁሶችና የምግብ ግበዓቶች ከቀሪ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ኮሚሽናችን ተረክቦ የቀድሞ ተዋጊዎች ላሉዋቸው ክልሎች የሚልካቸው ይሆናል።