ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች (CSO) ጋር ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የጋራ ምክክር መድረክ አዘጋጅቶ የግማሽ ቀን ውይይት አድርጓል።

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች (CSO) ጋር ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የጋራ ምክክር መድረክ አዘጋጅቶ የግማሽ ቀን ውይይት አድርጓል። በመድረኩ ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በመክፈቻ ንግግራቸው ኮሚሽኑ ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑንና በአጋርነትና ትብብር ረገድ ለጋሽ ባለድርሻ አካላት ጋር መምከርን ጨምሮ መሰል የምክክር መድረኮችን አዘጋጅቶ በመወያየት የኮሚሽኑን ዓላማና ተልዕኮ፣ ባለድርሻ አካላትንና ሚናቸውን፣ አጋርነትና ትብብር የተሃድሶ ፕሮግራሙ ቁልፍ ስራ መሆኑ ላይ ሰፊ ግንዛቤ በማስጨበጥ የሰላም ሂደቱ በዘላቂነት አስተማማኝ መሠረት ላይ እንዲተከል ዕቅድ አውጥቶ እየሰራና አጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ ይህም መድረክ አንዱ መሆኑን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከዚህ መድረክ ግንዛቤ በመነሳት ለሰላም ሂደቱ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን ተግባራት ለመለየት የጋራ task force አቋቁሞ በጥናት በመለየት ወደ ተጨባጭ ስራ መግባት እንደሚገባ አስምረውበታል። ለመድረኩ ዝግጅት ድጋፍ ያደረገው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሽፈራውም ባስተላለፉት መልዕክት ይህንኑ አጠናክረዋል። በመድረኩ በUNDP የDDR አማካሪ Mr. Basil Massy በተሃድሶ ፕሮግራም እሳቤዎች እንዲሁም የኮሚሽነር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሻንቆ ደለለኝም በኮሚሽኑ ተልዕኮዎች፣ አደረጃጀት፣ የባለድርሻ አካላትና ከCSO ስለሚጠበቅ አጋርነትና ትብብር ያዘጋጁትን ጽሑፍ አቅርበዋል። ሰፊ ውይይትም ተካሂዶ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በኩል እያንዳንዱ ድርጅት ሊያደርግ ስለሚችለው አስተዋፅዖ ተመካክሮ የጥናት ውጤቱን ለኮሚሽኑ በማቅረብ ወደ ቀጣይ ስራ እንደሚገባ መስማማት ላይ ተደርሷል።