የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ቤተሰቦች 17ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን አከበሩ

ጥቅምት 4 ቀን 2017ዓ.ም (ብ/ተ/ኮ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ቤተሰቦች በ17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2017ዓ.ም ሰንደቅ አላማ በመስቀልና ሀገራዊ ተልዕኳቸውን ለመተግበር ቃል በመግባት አክብረዋል፡፡
በእለቱ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ሀገራዊ ተልዕኳችንን ለመወጣት በአንድነትና በጋራ ስሜት በመተባበር ለሰላም፣ ለልማትና ለብልጽግናችን ስኬት ሁላችንም መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ የሚተገብረው የDDR ፕሮግራም ትኩረት ከተሰጣቸው ሀገራዊ እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑን ኮሚሽነሩ ጠቅሰው ቃላችንን በተግባር በማረጋገጥ በቀጣይ በስኬት ጭምር ታጅበን ሰንደቅ አላማችንን በክብር ከፍ የምናደርግበት ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በእለቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ሰንደቅ አላማ የመስቀል እና ቃል የመግባት ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡