“የአሜሪካ መንግስት ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት እንዲሳኩ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል” አምባሳደር ማይክ ሀመር



የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽር ተመስገን ጥላሁን የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡

ኮሚሽነር ተመስገን የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለማሳካት የዝግጅት ምእራፍ ስራዎች እና የመጀመሪያ ዙር DDR የቅድመ ትግበራ ስራዎችን ሂደት አብራርተዋል። የሀብት አሰባሰብ፣ አጋርነትና ትብብር ስራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለልዩ መልዕክተኛው ማይክ ሐመር ገልጸዋል። እስካሁን የአሜሪካ መንግስት እያደረገ ያለውን ድጋፍና ትብብር አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ ለማድረግና መልሶ ለማቋቋም እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቅ እና የትግበራ እንቅስቃሴ በመልካም ሂደት ላይ ነው ያሉት ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው የአሜሪካ መንግስት ፕሮግራሙ በታቀደው ጊዜ እንዲሳካ ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡