ክቡር የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ጋር በጽ/ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ተመስገን ከአምባሳደር ሚስተር ዳሪን ዌልች ጋር ባደረጉት ዉይይት የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመወጣት ያደረጋቸዉን ዋና ዋና ተግባራት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል ። በተጨማሪም የእንግሊዝ መንግስት ለፕሮግራሙ ማስፈፀሚያ ላደረገዉ የገንዘብ ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

ክቡር አምባሳደር ዳሪን በበኩላቸው ኮሚሽኑ ተልዕኮዉን ለመወጣት እያደረገ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ጥረት አድንቀዉ በቀጣይ የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራሙ እንዲሳካ የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል ።