ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ለተሀድሶ ቤተሰቦች የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ በመጀመሪያዉ ዙር ያዘጋጀዉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተሳተፉበት በቢሾፍቱ ከተማ አካሄደ ።

ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ለተሀድሶ ቤተሰቦች የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ በመጀመሪያዉ ዙር ያዘጋጀዉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተሳተፉበት በቢሾፍቱ ከተማ አካሄደ ።

ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በማቋቋሚያ ደንቡ የተሰጠዉ ተልዕኮ ሲጠቃለል… በተለያዩ መንገዶች ዓላማቸዉን በትጥቅ ሀይል ለማሳካት ተንቀሳቅሰዉ በመጨረሻም ከመንግስት ጋር በሚደረግ ስምምነት ትጥቃቸዉን አዉርደዉ ቀሪ ህይወታቸዉን በሰላማዊ መንገድ ለመምራት ፈቃደኛ የሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ በማድረግ መልሶ በዘላቂነት ማቋቋም ነዉ።

ይህንን አገራዊ የዘላቂ ሰላም ግንባታ አካል የሆነዉን ተልዕኮ ለማሳካት ኮሚሽኑ በሰባት ክልሎች 371,971 የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከ760 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚጠይቅ እና በሁለት ዓመታት የሚጠናቀቅ የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም እና ዝርዝር ማስፈፀሚያ ስልቶች ያዘጋጀ ሲሆን ከሰኔ 2016 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን ይጀምራል። በመጀመሪያው ዙርም 75ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከትግራይ ክልል በመጀመር ተግባራዊ ለማድረግ የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል ።

ይህንኑ ታሳቢ በማድረግም ከኮሚሽኑ ዋናዉ መ/ቤትና ከትግራይ ክልል ቅርንጫፍ የተዉጣጡና በየደረጃዉ የሚገኙ ከ60 በላይ አመራሮችና ፈፃሚ አካላት በተሳተፉበት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለመገንባት የሚረዱ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል ።

ስልጠናዎቹ ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ዝግጁነትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀዉ ” የተሀድሶ ቤተሰቦች የአቅም ግንባታ ስልጠና” መርሀግብር አካል ሲሆኑ በዚህ የመጀመሪያው ዙር ስልጠናዎች በኮሙኒኬሽን ፣ በአመራር ጥበብ እና በስነ-ልቦናና ጤና ላይ እንዲያተኩር ተደርገዉ የተዘጋጁ ናቸዉ።