ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሚስተር ቻ ሀን ዴንጎ ከኮሪያ ዓለምአቀፍ ትብብር አጄንሲ (KOICA) የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
በመጨረሻም በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል ሊኖሩ ስለሚገቡ የትብብርና አጋርነት መስኮችን እና የአፈፃፀም አግባቦችን በመለየት ከመግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን ሚስተር ቻ ሀን ለቀረቡ የአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ከዋና መ/ቤታቸው ጋር ተነጋግረው በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጡ አረ
ክቡር ከምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሚስተር ቻ ሀን ዴንጎ ከኮሪያ ዓለምአቀፍ ትብብር አጄንሲ (KOICA) የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
ክቡር አምባሳደር ተሾመ ሚስተር ቻ ሀን ዴንጎን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለዉ ባወያዩበት ወቅት የኮሪያ መንግስት ኮሚሽኑ ለጀመረዉ የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ስኬት የበኩላቸዉን ድጋፍ ለማድረግ ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዉ በተለይ በኮይካ(KOICA) በኩል ለቀድሞ ተዋጊዎች ምዝገባና ዲጅታል መታወቂያ ዝግጅት የሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እና የሙያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዉ ከቢሮዉ ዳይሬክተር በጎ ምላሽ አግኝተዋል ።
በመጨረሻም በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል ሊኖሩ ስለሚገቡ የትብብርና አጋርነት መስኮችን እና የአፈፃፀም አግባቦችን በመለየት ከመግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን ሚስተር ቻ ሀን ለቀረቡ የአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ከዋና መ/ቤታቸው ጋር ተነጋግረው በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል ።