የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀዉና በሁለተኛዉ የመካከለኛ ዘመን አገራዊ ፕሮግራም ላይ በተደረገ ምክክር የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ፕሮግራም ቀርቦ ግብዓት ተሰጥቷል።
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀዉና በሁለተኛዉ የመካከለኛ ዘመን አገራዊ ፕሮግራም ላይ በተደረገ ምክክር የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ፕሮግራም ቀርቦ ግብዓት ተሰጥቷል።
በፕላንና ልማት ሚኒስትር በክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በተመራዉ በዚህ መድረክ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን፣ የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና የገንዘብ ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። 23 አገራዊ የፖሊሲ ጉዳዮችን ማሳካትን ታሳቢ ባደረገዉ በዚህ በሁለተኛዉ የመካከለኛ ዘመን (2016-2018) ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋና የተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በዚህ መድረክ ክቡር አምባሳደር ተሾመ የኮሚሽን መ/ቤታቸዉ በትጥቅ ትግል ዓላማቸዉን ለማሳካት አስበዉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና ከመንግስት ጋር በሚደረግ የሰላም ስምምነት መሰረት ትጥቃቸዉን ፈተዉ ሰላማዊ ህይወት ለመምራት ፈቃደኛ የሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ በማድረግና መልሶ በማቋቋም የአገራዊ ሰላምና የልማት አቅም እንዲሆኑ ለማስቻል በ2015 መቋቋሙን ገልፀዉ በቀጣይ የኮሚሽኑን ተልዕኮ ለማሳካት የተዘጋጀዉን እና እ.ኤ.አ ከ2024 – 2026 ተግባራዊ የሚደረገዉን የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራሙን መሰረት አድርገዉ ለዉይይት መነሻ የሚሆኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አንስተዉ ምክክር ተደርጓል።
በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በአገር ደረጃ በሚተገበረው የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን ፕሮግራሙን ለማሳካት በጠቅላላው 767,517,449 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል። ከዚህ ዉስጥ 15% ማለትም 115,127, 617 የአሜሪካን ዶላር በመንግስት የሚሸፈን ሲሆን ቀሪዉን የአገር ዉስጥና የዉጭ የልማት አጋሮችን፣ ባለድርሻ አካላትን፣ የኢትዮጵያ ሰላም ወዳጆችን እና ምልዓተ ህዝቡን በማንቀሳቀስ እንደሚሸፈን በፕሮግራሙ ተመልክቷል ።