(ብ/ተ/ኮ የካቲት 9/2016) የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀዉና የለጋሽ አገራት አምባሳደሮች ፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሬታ፣ የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ተወካይ እና UNDP የኢትዮጵያ ተጠሪ በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ በማድረግ መልሶ የማቋቋም ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በጽ/ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል ።

በዚህ መድረክ ክቡር አምባሳደር ተሾመ ከአገር መከላከያና ከሚመለከታቸዉ ክልሎች ጋር በተደጋጋሚ በተደረጉ ዉይይቶች ከመግባባት የተደረሰባቸዉን 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ በማድረግ መልሶ የማቋቋም ስራዉን በአራት ምዕራፍ ለማጠናቀቅ የሚያስችል የፕሮግራም፣ ዝርዝር ፕሮጀክቶችና የሀብት ፍላጎት ሰነዶች እንዲሁም ተያያዥ የቅድመ ዲሞቢላይዜሽን የዝግጅት ምዕራፍ (Pre DDR) ስራዎች መጠናቀቃቸዉን ይፋ አድርገዉ ከልማት አጋሮች፣ ከኢትዮጵያ ወዳጆች እና ከመንግስት የሚጠበቁ የተግባር ምዕራፍ ጉዳዮችን አንስተዉ አብራርተዋል።
በዚህ የምክክር መድረክ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከመቀሌ በቀጥታ የስልክ መስመር በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ለፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት ተፈፃሚነት በፅናት መቆሙን በመግለፅ ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በሚያወጣው ፕሮግራም እና የአፈፃፀም ቅደም ተከተሎች መሰረት የክልሉ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዝ እንዲደረጉና መልሰዉ ተቋቁመው ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ።
የለጋሽ አገራት አምባሳደሮችና የተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በኮሚሽኑ የእስከአሁን የቅድመ ዲሞቢላይዜሽን የዝግጅት ምዕራፍ የተሳካ አፈፃፀምና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለፕሮግራሙ ስኬት ያለዉን ከፍተኛ ተነሳሽነት ከግንዛቤ በማስገባት ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
በመጨረሻም ሁሉም የምክክር መድረኩ ተሳታፊ ወገኖች የኮሚሽኑ ተልዕኮ በተቀመጠዉ የአፈፃፀም ምዕራፍና ቅደም ተከተል እንዲፈፀም የበኩላቸውን ድርሻ በተግባር ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል ።