የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ”ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል ርዕስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን አውደ ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ዲፕሎማሲያችን ከንግሥተ ሣባ ዘመን ጀምሮ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከተመሰረተበት 1900 ዓ.ም ያለዉን የሚዳስስ ሰፊና አስደማሚ ምዕራፎች ማየት ተችሏል።

በመቀጠልም ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቋቋም ጀምሮ እስከአሁን በዲፕሎማሲ ረገድ አገራችን የተጓዘባቸውን ርቀቶች ሠራተኛው እንዲገነዘብ ሆኗል፡፡

በዚህም በአገራችን መንግስታት ቢቀያየሩም ብሄራዊ ጥቅማችንን ማዕከል ያደረገዉና በቀጣናዉ፣ በአህጉሩና በዓለምአቀፍ ጉዳዮች የያዝናቸዉ ወጥ አቋሞች ለአሁኑም ሆነ ለቀጣይ ትዉልዶች ትምህርት ሰጪ እንደሆነ መረዳት ተችሏል ።