የጃፓን መንግስት የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት እንዲሳኩ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳወቀ ::
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሰደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር በጽ/ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።
ክቡር ኮሚሽነር ተመስገን ለአምባሳደር ሺባታ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመወጣት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት፣ የአጋርነትና ትብብር መስኮችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል።
ከዚሁ ጋር በማያያዝም የጃፓን መንግስት ከዚህ በፊት ለፕሮግራሙ ማስፈፀሚያ ላደረጋቸው ድጋፎች አመስግነው በቀጣይ የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራሙ በታቀደዉ መሰረት እንዲሳካ ትብብሩና ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነር ተመስገን ጠይቀዋል።
አምባሳደር ሺባታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ተልዕኮዉን ለመወጣት እያደረገ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ጥረት አድንቀዉ በቀጣይም ለፕሮግራሙ ስኬት የጃፓን መንግስት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በድጋሚ አረጋግጠዋል።