የደቡብ ኮሪያ መንግስት ብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እየተገበራቸው ያሉ ስራዎችን እደግፋለሁ ሲል ገለጸ።
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡
ኮሚሽነር ተመስገን ኮሚሽኑ የተሰጡትን አገራዊ ተልዕኮዎች ለማሳካት የዝግጅት ምእራፍ ስራዎች እና የመጀመሪያ ዙር DDR የቅድመ ትግበራ ስራዎች ሂደት ያለበትን የአፈፃፀም ደረጃ ገልፀዉ ለፕሮግራሙ ትግበራ የሚያስፈልገው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ የደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
አምባሳደር ካንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ረዥም የወዳጅነት ታሪክ ያላቸው መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ ለማድረግና መልሶ ለማቋቋም የያዘዉ ፕሮግራም በታቀደው ጊዜ ዉስጥ እንዲሳካ ድጋፍና ትብብር እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡