ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር በገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀዉ እና የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች በተሰባሰቡበት የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች ቡድን (Development Partners Group – DPG) የጋራ መድረክ

ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር በገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀዉ እና የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች በተሰባሰቡበት የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች ቡድን (Development Partners Group – DPG) የጋራ መድረክ ላይ በመገኘት የኮሚሽኑን ተልዕኮ እና የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ዋና ዋና ጉዳዮች እና ከልማት አጋሮች በሚጠበቁ የትብብርና አጋርነት መስኮች ላይ የተመሰረተ ገለፃ አድርገዋል።
በመድረኩ የተገኙ የአገራትና የተቋማት ተወካዮች በክቡር ኮሚሽነር እና በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በወ/ሮ ሰመሪታ ስዋሰዉ ከተደረገላቸው ዝርዝር ማብራሪያ ላይ በመመርኮዝ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
በመጨረሻም በኮሚሽኑ በኩል የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ በማድረግ መልሶ ለማቋቋም እና በአገሪቱ ሰላምና ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘዉ ፕሮግራም እንዲሳካ የበኩላቸዉን ድርሻ እንደሚወጡ በድጋሚ አረጋግጠዋል ።