የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በDDR አተገባበር ዙሪያ በጋራ ለመስራት ምክክር አካሄደ፡፡
(አዲስ አበባ ታህሳስ 18 ቀን 2017ዓ.ም ብ/ተ/ኮ) ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በክልሉ ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀልና መልሶ ለማቋቋም (DDR) በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሄዷል፡፡
ምክክሩ ትኩረት ያደረገው በDDR አተገባበር ዙሪያ ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
በክልሉ ለፕሮግራሙ አተገባበር እንዲያግዝ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እቅድ፣ የፕሮግራም ይዘት፣ የአተገባበር ስልትና የባለድርሻ አካላት ሚና ምን መሆን አለበት በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በውይይት መድረኩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡