የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በአፋር ክልል የሚገኙና የሰላም ስምምነት የፈረሙ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከል ማስገባት ጀመረ
(አብዓላ ታህሳስ 9 ቀን 2017ዓ.ም ብ/ተ/ኮ) በአፋር ክልል በትጥቅ ይታገሉ የነበሩና ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ትጥቃቸውን ያስረከቡ 1 ሺህ 750 የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ሰልጠና ለመውሰድ አፋር ክልል አብዓላ ጊዜያዊ የተሃድሶ ማዕከል መግባት ጀመሩ፡፡
በዲሞብላይዜሽን ፕሮግራም ማስጀመሪያ ላይ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የፕሮግራም ዕቅድና ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል በላይ አበበ እንደገለጹት በአፋር ክልል ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች በተሰባሰቡበት ማዕከል ፕሮግራሙ መጀመሩን አረጋግጠው በስምምነቱና በፕሮግራሙ መሰረት በማዕከሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማረጋገጥ፣ የመመዝገብና ሲቪክስ ስልጠና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ ሥልጠናውን በአግባቡ ሲያጠናቅቁ ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል ሲቪል ሕይወት እንዲመሩ እና በቀጣይ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ ኮሚሽኑ ከክልሉ መስተዳድር፣ ከባለድርሻ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ገልፀዋል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን በመወከል ይህንን ስራ እያስተባበሩ ያሉት አቶ መሀመድ አሊ በበኩላቸው ክልሉ ለሰላም ቁርጠኛ አቋም በመውሰድ ከአፋር ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ታጣቂዎች ጋር ተስማምቷል፡፡ እነዚህን የቀድሞ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በመቀላቀልና በዘላቂነት በማቋቋም የልማት አጋር እንዲሆኑ ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጋር በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችም የድርሻሁን አንድትወጡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በተሃድሶ ፕሮግራሙ እየተሳተፉ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች በበኩላቸው “ሰላም የማይተካ ሚና አለው፤ ከጦርነት ይልቅ ልማት ላይ ማተኮር ይገባናል፤ ችግሮችን በሰላዊ መንገድ መፍታት አትራፊ ነው፤ ከተሃድሶ ስልጠና በኋላ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የልማት አጋርነታችንን እናረጋግጣለን” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በተሃድሶ ፕሮግራሙ እየተሳተፉ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች በበኩላቸው “ሰላም የማይተካ ሚና አለው፤ ከጦርነት ይልቅ ልማት ላይ ማተኮር ይገባናል፤ ችግሮችን በሰላዊ መንገድ መፍታት አትራፊ ነው፤ ከተሃድሶ ስልጠና በኋላ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የልማት አጋርነታችንን እናረጋግጣለን” ሲሉ አስተያ