“የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸዉ ያሉት የ DDR ሁሉንአቀፍ የቅድመ-ዝግጅት እና ፈፃሚ ተቋም የመገንባት ስራዎች አበረታች ናቸዉ፡፡” የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ።
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና አመራሮች በቅርቡ ከተሾሙት ከመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ጋር ስለ ተቋሙ አጠቃላይ እንቅስቃሴና እየተከናወኑ ባሉ የDDR ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ሚኒስቴር ሆኖ መቋቋሙን እና በጋራ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ ለማድረግና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል አገራዊ ፕሮግራም፣ ፕሮጅክቶችን እና ማስፈፀሚያ ማንዋሎች ቀርጾ ወደ ተግባር በመግባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወኑን ገልፀዉ ፕሮግራሙ ከፍተኛ ሀብትና ቅንጅታዊ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ ሀብት ለማሰባሰብ እንዲሁም ተቋሙን ለማጠናከር የመከላከያ ሚኒስቴር ድጋፍና እገዛ ያስፈልገናል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
“የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸዉ ያሉት የ DDR ሁሉንአቀፍ የቅድመ-ዝግጅት እና ፈፃሚ ተቋም የመገንባት ስራዎች አበረታች ናቸዉ” ያሉት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ፕሮግራሙ በታቀደው ጊዜ በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተልዕኮ፣ አጠቃላይ ፕርግራም ፣ ፕሮጅክቶች እና ዝርዘር የአተገባበር እቅድና ዝግጅት እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ቀጣይ የትኩረት መስኮች በዝርዘር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡