የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋራ ለመስራት ምክክር አካሄዱ፡፡

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተልዕኳቸዉ አኳያ በጋራ ሊከናወኑና ሊተገበሩ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለቱም ኮሚሽኖች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በጋራ መክረዋል፡፡

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንደገለጹት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ ለማድረግ፣ የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት መልሶ ለማቋቋምና ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችና ምክክሮችን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው የሀገራዊ ምክክር ፋይዳው አካታች ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ነው፡፡ ለሀገራዊ ሰላምና መግባባት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጋር በትብብር፣ በአጋርነትና በመናበብ ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡