ክቡር ኮሚሽነር የዴንማርክ አምባሳደርን አነጋገሩ!
ኮሚሽነር የተከበሩ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የዴንማርክ አምባሳደር ክብርት ኪራ ስሚዝ ሲንድብጀርግን ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ውይይቱ በአጋርነትና ትብብሮች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ያከናወናቸው ተግባራት፣ ከቀድሞ ተዋጊዎች ቁጥር አንጻር የተሃድሶ ፕሮግሙ ከፍተኛ ወጪ የጠየቀ መሆኑ፣ ፕሮግራሙ ውስብስብ፣ ጥንቃቄ የሚሻና በፍጥነት መከናወን የሚገባው መሆኑ፣ የፕሮግራሙ መጓተት በቀድሞ ተዋጊዎቹ ላይ እያሳደረ ስላለው መሰላቸትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት በፀጥታና ደህንነት ረገድ ስጋት ሊፈጥር የሚችል መሆኑ፣ በመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) አስተባባሪነት እየተከናወነ ያለው የፕሮግሙ ሃብት ማሰባሰብ ሂደት መጓተቱ፣ ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ከዴንማርክ መንግስት ጋር ስላሉ የሁለትዮሽ የልማት ፕሮግራሞች ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
የዴንማርክ አምባሳደር ክብርት ኪራ ስሚዝ ሲንድብጀርግን ግጭቶች የሰላም ሂደቱን እንዳያደናቅፉ ሊደረግ በሚገባው አገራዊ ምክክር መንግስታቸው ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለ ያለ መሆኑንና የመንግስታቸው ዓመታዊ የልማት ድጋፍ በጀት ዝግጅትና የዝግጅቱ ወቆቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽነር የተከበሩ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በበኩላቸውም በፖለቲካዊ መግባባቶች፣ በደህንነትና መተማመኖች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል በጋራ በመረባረብ በተቻለ ፍጥነት የተሃድሶ ፕሮግራሙን የማስጀመር አስፈላጊነት ላይ አስምረው አሳስበዋል፡፡
The Commissioner discussed DDR issues with the Danish Ambassador!
Commissioner H.E. Ambassador Teshome Toga, discussed H.E. Kira Smith Sindbjerg, Danish Ambassador to Ethiopia, Djibouti, South Sudan and Sudan, Permanent Representative to the African Union, IGAD and UNECA, on Thursday 16th November, 2023, at his good office, wherein they exchanged views on partnership and cooperation on the DDR program. Issues of the commission activities, the expensiveness, the complexity, sensitivity and urgency of the program, the challenges and fear of security alertness about the developing frustration among former combatants, the mere fact of the delay of the program, the slow basket fund processes, the current national situation vis-a-vis the status of the program, bilateral issues with the Danish development programs.
H.E. Ambassador Kira, stressed the Danish government’s concern over increasing the dialogue processes over conflicts that are trading-off the peace processes. She also highlighted the modality of the Danish annual budget program and the time frame for due consideration. While Commissioner H.E. Ambassador Teshome Toga, on his part, pressed on the urgency of the start of the program activities, which would otherwise may have a negative impact politically on the consented buy-in trust and on security matters.