ክቡር ኮሚሽነር ከአጋሮች ጋር ውይይት አደረጉ!
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር የተከበሩ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ ከኢትዮጵያ የሰላምና የልማት አጋር አገራት ኤምባሲዎችና ተቋማት ተወካዮች ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ።
የተከበሩ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኮሚሽኑ አጠቃላይ ተልዕኮ አድማስና የሚጠበቁ ውጤቶች እንዲሁም ከአጭር ጊዜ አኳያ በመጀመሪያው ምዕራፍ ዲሞቢላይዝ የሚደረጉና መልሰው ወደ ማህበረሰቡ ለሚቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎች በሚመለከት ከአጋሮች በሚጠበቀው ድጋፍና የአፈፃፀም አግባቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ከገለፃው በኋላም ኤምባሲዎችንና ተቋማትን ወክለው የተገኙት በኮሚሽኑ ተልዕኮ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን በሚመለከቱና በድጋፉ አጠቃቀም ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። በመጨረሻም ተሰብሳቢዎች ለተሰጣቸው ማብራሪያ ምስጋና አቅርበው በኢትዮጵያ ሰላምና ልማት በአጠቃላይ እንዲሁም የኮሚሽኑ ተልዕኮዎች በተለይ እንዲሳኩ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል ።