ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከፊንላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ!
ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከፊንላንድ አምባሳደር ክብርት ሲኒካ አንቲላ ጋር በቢሯቸው ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተሃድሶው ፕሮግራም ዙሪያ ስላሉ የውስጥና የውጭ አጋሮች ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅና የቀድሞ ተዋጊዎች በተሃድሶው ላይ የጣሉት ከፍተኛ ተስፋ በፕሮግራሙ መጓተት ሳቢያ ወደ ተስፋ መቁረጥና መሰላቸት የመለወጥ ያልተጠበቀ ስጋት ሊፈጥር እንደሚችልም አሳስበዋል፡፡ በትግራይ ካሉ 274,000 የቀድሞ ተዋጊዎች 70% የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ30 በታች ሲሆኑ፣ በተጨማሪም 70% የሚሆኑት ተዋጊ ከመሆናቸው በፊት ስራ የሌላቸው የነበሩ በመሆኑ የተሃድሶ ፕሮግራሙ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ እንደ ስጋት ከሚታዩ ጉዳዮች መካከል የተወሰኑት የቀድሞ ተዋጊ ወጣቶች ሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ አህጉር እየተንቀሳቀሱ እንዳለና ይህም አውሮፓውያን ላለባቸው የስደተኛ ቀውስ ተጨማሪ ስጋት የሚፈጥር ፈታኝ ሁኔታ ነው ብለዋል፡፡
የፊንላንድ አምባሳደር የተከበሩ ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸውም የተሃድሶ ፕሮግራሙ ውስብስብና የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ያሉበት በመሆኑ አሳሳቢና አገራቸው ለሰላም ሂደቱ ወሳኝ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፊላንድ መንግስት በኢትዮጵያ እያከናወነ ስላለው የትምህርት፣ የግብርና፣ የውሃ፣ የመሬት አስተዳደር፣ የብሔራዊ ዕርቅ ፕሮጀክቶች ጠቁመው፣ የተሃድሶ ፕሮግራሙን በመደገፍ ረገድ በተያዘው 2023 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀቱ ስራ ላይ የዋለና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ክፍተት ባይኖርም፣ ለቀጣዩ 2024 በጀት ዓመት ስለተያዙ ቀዳሚ የፕሮጀክት ትኩረቶች ዙሪያ ከልማት ፕሮግራም ባለሙያዎቻቸው ጋር እንደሚመክሩበት አስታውቀዋል፡፡
The Commissioner exchanged views with the Finnish Ambassador!
At the discussion held on 20th November, 2023, Commissioner H.E. Ambassador Teshome Toga, informed the Finnish Ambassador H.E. Sinikka Antila, about the international and local partnership regarding the DDR program. In due course, he stressed the high cost of the DDR and the risk of high expectations of the former combatants resulting from boredom and frustration about a delayed DDR program. He noted that, of 274,000 former combatants in Tigray, 70% are below 30 years old, and again 70% were unemployed in their former life before the war. Due to the delay of the program, some of them have started crossing the Mediterranean Sea into Europe, which may add burden to the existing European migration crisis and active labour drain in their home land. In effect, it implied the role of the DDR program for political, economic and social stabilization is meaningful.
Finnish Ambassador H.E. Sinikka Antila, explained her concern over the dynamism and complexity of the DDR program, and confirmed that the Finnish government supports the Secession of Hostility Agreement to strengthen the peace process. She also addressed the on-going traditional cooperation programs in Ethiopia like education, agriculture, water, land management and now the national dialogue. On matters related to the DDR program, H.E. Sinikka said she will take it for consultation with the development program team members at the Embassy to clarify prior projects in 2024, reminding the program budget for 2023 is in operation that funding the DDR program is constrained by on-going projects.