ከአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር ውይይት ተደረገ!
ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት የምክር ቤቱዋና ፀሐፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም፣ የግልግል ተቋም ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወ/ገብርኤል እና የዋና ፀሐፊው አማካሪ አቶ ሲሳይ ታደሰ ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱ ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በሰጡት ማብራሪያ የሰሜኑ ጦርነት በግሉ ዘርፍ ስላሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ፋይዳ፣ የኮሚሽኑ መቋቋምና ተግባራቶቹ፣ ስለተዘጋጀው የፕሮግራም ፕሮጀክት ሰነድና ኮሚሽኑ ስለሚያስፈልጉት የአቅም ግንባታ ድጋፎች፣ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገራት አጋሮችና ለጋሾች ጋር እየተደረጉ ስላሉ የድጋፍና ትብብር ውይይቶች፣ የግሉ ዘርፍ በፕሮግራሙ መሳተፍ በተለይም የፕሮግራሙን ስራዎች በማስተዋወቅ፣ የቴክኒክ፣ የማቴሪያልና የፋይናንስ ሃብት በማሰባሰብ፣ በስልጠና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ስለሚኖረው ሚና አጉልተው ሃሳባቸውን አጋርተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አመራሮችም ለውይይት መጋበዛቸው እንዳስደሰታቸው፣ ኮሚሽኑን ስራ መደገፍ እንደሚፈልጉና እንደሚገባ፣ በዚህ ረገድ የፕሮግራሙን ስራዎች ለማስተዋወቅ፣ ለስልጠና ፕሮግራሙ ድጋፍ ማድረግ የሚችል የስልጠና ማዕከል እንዳላቸው፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ተባብረው መስራት እንደሚችሉና በዚህ ረገድ ከስራና ክልሎት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ጋር እየሰሩ ስለመሆኑ፣ የፋይናንስ ሃብትም ለማሰባሰብ እገዛ እንደሚያደርጉ፣ በአጠቃላይ በሰላም አስፈላጊነቱ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በማጠቃለያም ቀጣይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ በጋራ ለመስራት በሚያስችለው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድና ስምምነቱን ለማስፈጸም የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ዙሪያ ለመወያየት ስምምነት ተደርጓል፡፡
A discussion was held with the Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations!
Secretary General of the Council Mr. Shibeshi Betemariam, Director of the Arbitration Institute Mr. Yohannes W/Gabriel and Mr. Sisay Tadese, Advisor to the Secretary General were present at the meeting with the Commissioner H.E. Ambassador Teshome Toga held on 22nd November, 2023. During the discussion, the Commissioner H.E. Ambassador Teshome Toga gave an explanation about the negative impact of the war in the northern Ethiopia on the private sector, the benefits of the ceasefire agreement, the establishment of the commission and its activities, the prepared program project document and the capacity building support needed by the commission, a discussions being held with local and international partners and donors, the participation of the private sector in the program, especially its role of promoting the program, training, job creation, gathering technical, material and financial resources.
The leaders of the council said that they were pleased to be invited to the discussion, that they want and should support the work of the commission. They stated that they can promote the program’s activities, have a training center to support the training programs. They added that they can work together in creating job opportunities while noting they are working with the Ministry of Labor and Skill. They also engage in resource mobilization.
In conclusion, it was agreed to set up the next consultative meeting and discuss the document of the Memorandum of Understanding and the preparation of the action plan to implement the agreement.