ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለኮሚሽኑ አዳዲስ የአመራር ሹመቶች ተሰጡ። በበላይነት የሚመራዉ ቦርድም ተሰየመ።

ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በግል ጉዳያቸዉ ምክንያት በኮሚሽነርነት ላለመቀጠል ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት በማግኘቱ የኮሚሽነርነት ቦታቸዉን ከመጋቢት 3/2016 ጀምሮ ለቀዋል።

በምትካቸዉ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ክቡር አቶ ተመስገን ጥላሁን የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል።

የኮሚሽኑ የሎጂስቲክስ እና አስተዳደር ዘርፍ ም/ኮሚሽነር በሆኑት በዶ/ር አትንኩት መዝገበ ምትክ ክቡር አቶ ተስፋዓለም ይህደጎ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተሹመዋል ።

በተጨማሪም ኮሚሽኑን በበላይነት የሚመራ በፍትህ ሚኒስትሩ በክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የሚመራ እና አምስት ከፍተኛ አመራሮች አባል እንዲሁም ክቡር ኮሚሽነር ፀሀፊ የሆኑበት ቦርድ ተሰይሞለታል።

መላዉ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ቤተሰቦች ለተሰናባቾችም ሆነ አዲስ ለተመደቡ አመራሮቻችን መልካም የስራ ጊዜን እንመኛለን ።