ነገን ዛሬ እንትከል።
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ነገን ዛሬ እንትከል በሚለው መሪ ቃል የሰላም ሚኒስቴርና የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክ 2000 ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ይኸው አገራዊ፣ ቀጠናዊ አልፎም ዓለም አቀፋዊ ፋይዳው አንፀባራቂ መሆኑን ያሰመሩበት ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ እያስተናገደች ያለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ የሰው ልጅን የመኖር ህልውና እየተፈታተነ ይገኛል ብለዋል። ይህ የአረንጓዴ አሻራ ተልዕኮ የህዝባችንን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ አካባቢያችንን ምቹ መኖሪያ ለማድረግ፣ ቀጠናዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችል አኩሪ ታሪካዊ ተግባር መሆኑንም ገልፀዋል። አያይዘውም ዛሬ 2000 ችግኞችን በመትከላችን ብቻ ሳንዘናጋ ደጋግመን በመምጣት በመንከባከብ ፀድቆ ልናየው ይገባል በማለትም አሳስበዋል።