ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የጥቅምት ወር ወርሃዊ ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ!
ኮሚሽኑ የ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የጥቅምት ወር ወርሃዊ ዕቅድ አፈጻጸሙን ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የገመገመ ሲሆን፣ ግምገማው የ3ቱን ዘርፎች ማለትም የኮሚሽነር ጽ/ቤት፣ የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ እና የሎጂስቲክና አስተዳደር ዘርፎችን ያካተተ ነው። ሪፖርቱ በስትራተጂክ ጉዳዬች ስራ አስፈፃሚ የቀረበና ውይይት የተካሄደበት ሲሆን፣ ግምገማውን የመሩት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ብ/ጄኔራል ደርቤ መኩሪያ የኮሚሽኑ አፈጻጸምና ሪፖርት አቀራረብ ከባለፉት ወራት የተሻለ ለውጥ ማሳየቱን ገልጸዋል። የውይይት መድረክም ከፍተው ሰራተኛው የተለያዩ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርቦ በክቡር ምክትል ኮሚሽነርና የየዘርፉ የበላይ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። የቀጣዩ ወር ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች፣ ተግባራትና በሚጠበቁ ውጤቶች አቅጣጫ ተይዞባቸዋል። በዕለቱ ሁለተኛ አጀንዳ ሆኖ በቀረበው የኮሚሽኑ የተጠሪነት ለውጥ ዙሪያ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ብ/ጄኔራል ደርቤ መኩሪያ ሰራተኛው ተገቢውን ግንዛቤ በሚጨብጥበት አግባብ መረጃዎችን ሰጥተዋል።