ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከዩ.ኤን.ዲፒ ጋር በመተባበር ለሰራኞቹ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ!
በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንና በዩ.ኤን.ዲፒ ትብብር ከጥቅምት19 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ለኮሚሽኑና ለትግራይ ቅ/ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ሰጠ። በሥልጠናው የኮሚሽኑ የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊንና 2 ባለሙያዎችን ጨምሮ 28 ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ ስልጠናው በውጤት ተኮር ሥራ አመራር የተቃኘ ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ፣ የፋይናንስ አስተዳደር የፕሮግራም አተገባበር ማንዋል እና የግዢ ሥርዓት የያዘ ነበር። ሥልጠናው የዩ.ኤን.ዲፒ ፈንድን ከማስተዳደር አኳያ የኮሚሽኑን ባለሙያዎች ውጤታማ እንደሚያደርግ ስልጠናውን የከፈቱት የዩ.ኤን.ዲፒ ምክትል ኃላፊ ሚስ ሃይን ዳንግ ገልፀዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዩ.ኤን.ዲፒ የክትትልና ግምገማ እንዲሁም የግዢ ስፔሺያሊስቶችና ኦፊሰሮች ናቸው።