ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ የቀድሞ ተዋጊዎች የአልባሳት፣ ጫማዎችና ምግቦች ድጋፍ አደረገ!
ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በድጋፍ ያገኛቸውን ዋጋቸው ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የአልባሳት፣ ጫማዎችና ምግቦች በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲውል ድጋፍ አድርጓል፡፡ ያቤሎና ሐዋሳ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ኮሚሽናችን የተረከባቸውን እነዚህኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በሻሸመኔ ለክልሉ ያስረከቡት የኮሚሽናችን ተወካይ አቶ ሽመልስ በላሶ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ በማቀላቀል ሰላማዊና ልማታዊ ኑሮ እንዲኖሩ ማስቻል የኮሚሽኑ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ድጋፍ የዚሁ ጥረት አካል ነው ብለዋል፡፡