በመቀሌ በምክክር ላይ የነበረው የDDR ባለድርሻ አካላት ቡድን የተመረጡ የምዝገባ ጣቢያዎችን ጎበኘ።

በክቡር ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን የተመራዉ ቡድን ኮሚሽኑ በመጀመሪያው ዙር ከትግራይ ክልል ዲሞቢላይዝ የሚያደርጋቸዉን የቀድሞ ተዋጊዎች ምዝገባ ለማካሄድ፣ የስነ ልቦና ድጋፍና የተሀድሶ ስልጠናዎች ለመስጠት እንዲቻል በክልሉ ከተለዩት አምስት ማዕከላት ዉስጥ የአጉላንና እዳጋ ሀሙስ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ማዕከላቱ በየዙሩ ለሚገቡ የቀድሞ ተዋጊዎች የመመዝገቢያ፣ የመመገቢያ፣ ስልጠና እና የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችና በአጭር ጊዜ መስተካከል የሚገባቸዉ ተግባራት የተለዩ ሲሆን በቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸዉ ተግባራት ላይም የጋራ መግባባት ተደርሷል።

በዚህ ጉብኝት የኮሚሽኑና የክልሉ አመራሮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ተገኝተዋል።