ሚስተር ከንሱኬ ኦሺማ የጃፓን ዓለምአቀፍ ትብብር (-Japan International Cooporation Agency – JICA) የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ዋና ተጠሪ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ተልዕኮዎች እንዲሳኩ የበኩላቸዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለፁ።
ሚስተር ከንሱኬ ኦሺማ የጃፓን ዓለምአቀፍ ትብብር (-Japan International Cooporation Agency – JICA) የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ዋና ተጠሪ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ተልዕኮዎች እንዲሳኩ የበኩላቸዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለፁ። ሚስቴር ከንሱኬ ይህን ያሉት ከብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ባደረጉት ምክክር ማጠቃለያ ነዉ።
ክቡር አምባሳደር ተሾመ ሚስተር ከንሱኬን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለዉ ባወያዩበት ወቅት የጃፓን መንግስት ለኮሚሽኑ የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ስኬት እያደረገ ላለዉ ሁሉንአቀፍ ድጋፍ አመስግነዉ በተለይ በጃይካ (JICA) በኩል ለቀድሞ ተዋጊዎች ምዝገባና ዲጅታል መታወቂያ ዝግጅት የሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እና የሙያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዉ ከዋና ተጠሪዉ በጎ ምላሽ አግኝተዋል ።
በመጨረሻም በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል ሊኖሩ ስለሚገቡ የትብብርና አጋርነት መስኮችን እና የአፈፃፀም አግባቦችን በመለየት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ።